=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ቂሎች እና ወራዶች የሁሉ ፈጣሪና መጋቢ የሆነውን አሏህ ሰድበዋል ፤ ብቸኛውን አምላክ ዘልፈዋል። ታዲያ ስህተትና ጉድለት መለያችን የሆንነው እኔ ፣ አንተና እኛ ምን እንጠብቃለን። በህይወትህ ውስጥ ርህራሄ የሌለበት ሐሰተኛና መራራ የትችት ፍልሚያ ሊያጋጥምህ ይችላል ፤ ሆን ተብሎና ተጠንቶ የሚደረግ የሞራል ክስከሳ ይደርስብህም ይሆናል ፤ የታለመ የማዋረድ ሙከራ ያጋጥምህም ይሆናል። ይህ ሁሉ ግን ሊደርስብህ የሚችለው የምትሰጥ ፣ የምትገነባ ፣ በሌሎች ላይ ተፅዕኖ መፍጠር የምትችል እና ከሌሎች የምትበልጥ ከሆንክ ነው። እነዚህ ሰዎች በምድር ውስጥ ዋሻ ቆፍረህ ካልተደበክ ወይም በሰማይ ላይ መሰላል አድርገህ ካልሸሸሃቸው በስተቀር አይተውህም። በመካከላቸው እስካለህ ድረስ የሚያስከፋህን የሚያስቅህን የሚያደማህን እና እንቅልፍ የሚነሳህን ድርጊት እንደሚፈፅሙብህ አትጠራጠር።
ምድር ላይ የተቀመጠ ሰው አይወድቅም ፤ ሰዎች የሞተን ውሻ በእግራቸው አይመቱም። በመልካምነት ፣ በእውቀት ፣ በስነ-ምግባር ወይም በገንዘብ ስለበለጥካቸው ይናደዱብሃል። ባንተ ላይ ያሉትን የአሏህ ፀጋዎች እና ችሎታዎችህን እስካልተውክ ድረስ አንተ እነርሱ ዘንድ ወንጀለኛ ነህ። ምስጉን የሆነ ባህርያትን እስካልተውክ ፤ የተወደዱ ስነ-ምግባራትን በሙሉ አውልቀህ ካልጣልክ እና ጅል ፣ ደደብ ፣ ሰባራ ፣ ዜሮና ቦታ የሌለህ እስካልሆንክ ድረስ አይቀበሉህም። በትክክልም የሚፈልጉት ይህንን ነው። ስለዚህ የነዚህን ሰዎች ንግግር ፣ ትችታቸውን ፣ የስም ማጥፋት ዘመቻቸውን እና አንተን የማዋረድ ሙከራቸውን አትሸነፍለት። የበረዶ ፍሬዎች ሲወድቁባት የሚሰባበሩ ዝምተኛና ትልቅ አለት መስለህ ኑር። የተችዎችህን ንግግር ከሰማህና ተፅዕኖም ካሳደረብህ ህይወትህን የማደፍረስና የማቆሸሽ ርካሹን ምኞታቸውን ታሳካላቸዋለህ። ንቃ!......... መልካምን ይቅርታ አድርግላቸው፤ ንቃ!........ ፊትህን አዙርባቸው ለሚያሴሩትም ደባ አትጨነቅ ውድቁ ትችታቸው በላጭነትህን አመላካች ነው። በማህበረሰብህ ውስጥ ባለህ ክብደትና በላጭነት ያህል ትችቶች ይበዙበሃል።
በእርግጥ አንተ የነዚህን ሰዎች አፍ መዝጋት አትችልም ፤ ምላሾቻቸውንም ማሰር አትችልም ፤ ባይሆን ትችታቸውን መቅበር ትችላለህ። ከነሱም በመራቅህ ፣ እነሱን ችላ በማለትህ እና ንግግራቸውን ዘወር ብለህ ባለመስማትህ ፣ ጥሩ ስራዎችን በማብዛት ፣ መልካም ምግባሮችህን በማሳደግ እና ስህተትህን በማረም ዝም ልታስብላቸው ትችላለህ።
ሁሉም ዘንድ ተወዳጅና ተቀባይነት ያለህ ፤ እንዲሁም ከነውር የነፃ መሆን የምትፈልግ ከሆነ በፍፁም የማይቻልን ነገር ሽተሃል ፤ የማይደርስበትንም ምኞት ተመኝተሃል።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|